Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሶማሌ ክልል የሠንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው በዓል ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አንድነትና ህልውናችንን ያረጋገጥንበት ቀን ነው ብለዋል።

ቀኑን ስናከብር ሠንደቅ ዓላማችን በከፍታ እንዲውለበለብ የተደረገውን ትግል በመዘከር ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

ሠንደቅ ዓላማችንን የመጠበቅ፣ የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ሲሉም ነው የገለፁት።

ባለፉት ሰባት ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶችን ለማስቀጠል በአንድነትና በህብረት ሆነን ሁላችንም መረባረብ ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Exit mobile version