አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሀሳብ በተከበረው በዓል ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዛሬው ትውልድ የአባቶቹን ፈለግ በመከተል በሠንደቅ ዓላማ ስር በመሰባሰብ የልማት አርበኛነቱን እያስመሰከረ ይገኛል ብለዋል።
ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለማስወገድ እንዲሁም ሀገርን ወደ ብልጽግና ማማ ለማውጣት ትውልዱ ሜጋ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ወደ ሥራ ከማስገባት ጀምሮ የተለያዩ ውጤታማ ሥራዎችን በማሳካት ላይ ይገኛል ነው ያሉት።