አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሙስናን መዋጋት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ።
የክልሉ የመንግሥት እና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች ካለው የመልማት አቅም እና ፍላጎት አንፃር አሁንም ብዙ ይቀራል።
ከሀገር እስከ ግለሰብ የተረጋገጠ ብልፅግናን ለማምጣት የሕዝቡን የቁጠባ ባህል ማሳደግ፣ የወልና የግል አቅም በትክክል መጠቀም፣ ፈጣን የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ስራዎች ሊሰራ የሚገባቸው መሆኑን አንስተዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት የተከናወኑ ሰራዎች በመድረኩ በጥልቀት ሊገመገሙ አና እያንዳንዱ አመራር ራሱን ሊያይበት እንደሚገባም አሳስበዋል።
በክልል ደረጃ የዜጎችን የልማት እና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ሙስናን የመዋጋት፣ የስራ አጥ ቅነሳ፣ ድህነትን መዋጋት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ በመድረኩ ላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው÷ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች የመለሱ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
“አንድ ዓመትን እንደ አምስት ዓመት በማሰብ እንስራ” በሚል እቅድ በመንቀሳቀስ ሰላምን የማረጋገጥና አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ሂዴት ላይ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ በየደረጃው ያሉ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በሚልኪያስ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!