አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጂቡቲ ሪፐብሊክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል ቃለ መኃላ ፈጽመዋል።
አምባሳደሩ ከፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን በመቀበል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ፊት ቀርበው ነው ቃለ መኃላ የፈጸሙት።
ፕሬዚዳንት ታዬ ለተሿሚ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና ጂቡቲን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ መታደማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!