Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ የተሰኘ አዲስ የስልክና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ የተሰኘ የስልክ ቀፎ እና አዳዲስ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች መለያን ይፋ አድርጓል።
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ተቋማቸው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ የቴሌኮም ማስፋፊያዎችን እያደረገ ይገኛል።
ኢትዮ ቴሌኮም ቀደም ሲል እንደ 4ጂ እና 5ጂ፣ ቴሌ ብር፣ ቴሌ ገበያ እና ሌሎች የዲጂታል አማራጮችን ይፋ ማድረጉን አስታውሰው፥ በዚህም በዲጂታል ኢኮኖሚው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው በቀጣዩ ሦስት አመታት “ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር” በሚል መሪ ቃል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ዘኔክሰስ ቴክኖሎጂ የዚህ እቅድ አካል መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
ዘኔክሰስ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በቴሌ ክላውድ ብቻ የሚተዳደርና በርካታ መተግበሪያዎች ያሏቸው ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎችና ኮምፒውተሮችን ያካተተ ነው።
አዳዲሶቹ የኔክሰስ ምርቶች የ4ኛው ትውልድ ኔትዎርክ የተገጠመላቸውና በተመጣጣኝ ገንዘብ ለተገልጋዮች የሚቀርቡ ሲሆን፥ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በር ከፋች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version