Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ አህመድ ሺዴ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ከአይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን አቪዬሽን ዘርፍ እንዲሁም የኢኮኖሚ ልማት ግቦችን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ነው የመከሩት፡፡

በውይይታቸውም በቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገነባው ግዙፉ የዓለም አቀፍ አውሮፕላን ፕሮጀክት ፋይናንስ ለማድረግ እና ለማዋቀር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የመንገደኞችን እና የጭነት አቅምን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ያለውን መጨናነቅ በማቃለል ለአፍሪካ ቀንድ ዋና የሎጂስቲክስ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተመላከተው፡፡

አቶ አሕመድ ሽዴ ውይይቱ ለሕዝባችን እና ለኢኮኖሚያችን የረጅም ጊዜ ጥቅሞችን የሚያመጣ ጠንካራ አጋርነት ለመገንባት ጠቃሚ ርምጃ ነው ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን በገንዘብ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ ልማት አቅርቦት እና በግንባታ ለመደገፍ ያለውን ፍላጎት ገልጿል፡፡

ለአዲሱ የዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ምቹ የሆነ የፋይናንስ መዋቅር ለማዘጋጀት ሁለቱም ወገኖች ትብብራቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡

ውይይቱ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማራመድ የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ ጠንካራ አጋርነትና የጋራ ራዕይን ለማሳካት እንደሚያግዝ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶች ላይ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን የሚያስገኙ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ የጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ፕሮጀክቶችን ያካተተ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version