Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የስፖርት ዘርፉን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ አወሉ አብዲ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ የስፖርት ዘርፉን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ፡፡

20ኛው የኦሮሚያ ስፖርት ምክር ቤት ጉባዔ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ አወሉ አብዲ በመድረኩ እንዳሉት÷ እንደ ሀገር ለስፖርት ዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት ተከትሎ የክልሉ መንግስት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለማስፋፋት በሰራቸው ስራዎች ስኬቶች ተመዝግበዋል።

 

በኢትዮጵያ ትልቅ እና የስፖርት ዘርፍ ምልክት የሆነው አትሌቲክስ ዳግም እንዲያንሰራራ የክልሉ ስፖርት ጉባዔ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

 

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ቢያ በበኩላቸው÷ የክልሉ መንግስት ከስፖርት ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ክልሉ የጠንካራ ስፖርተኞች ማዕከል መሆኑን ጠቅሰው÷ በሁሉም የስፖርት አይነቶች በርካታ ወጣት ስፖርተኞችን ለሀገር ማበርከት መቻሉን ጠቁመዋል።

ጉባዔው የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምን ከመገምገም ባለፈ የ2018 በጀት ዓመት የስራ ማስፈጸሚያ በጀት እና ዕቅድን ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በመራኦል ከድር

Exit mobile version