አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለባቡር መሰረተ ልማት ሥራዎች ትልቅ ዕድል ነው አሉ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስለሺ ካሳ።
አቶ ስለሺ እንዳሉት÷ የሕዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ ለሚገኙ የባቡር መስመሮችና በቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች መስመሮችን ለመዘርጋት የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት እድሎችን ያሰፋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ስምንት መስመሮችን በመዘርጋት የባቡር መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ማቀዱን አመልተዋል፡፡
እነዚህ ግንባታዎች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘን በባቡር መሰረተ ልማት የተሳሰረች እንደምትሆን ነው የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያ በአማራጭ ወደቦች ተጠቃሚ እንድትሆን የሚከናወኑ ሥራዎችን ማሳለጥ እንዲቻል ከምርት ስፍራ እስከ ወደብ የሚያስተሳስሩ የባቡር መሰረተ ልማቶችን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን ከደረቅ ወደብ ጋር በባቡር መሰረተ ልማት ማስተሳሰር መቻሉን አንስተው÷ በቀጣይ የሚኖሩ የንግድ ቀጣናዎችን ታሳቢ በማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የባቡር ዘርፍ እድገቱን ለማሳለጥ ከቻይና፣ ጀርመንና ደቡብ ኮሪያ ቴክኒካል ድጋፍ ለማግኘትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።
በቀጣይ የሚሰሩ የባቡር መሰረተ ልማቶችን 80 በመቶ የሚሆነውን በራስ አቅም ለመስራት ታቅዶ ክፍሎችን የማደራጀትና የሙከራ ፕሮጀክት ትግበራ መጀመሩን ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!