Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጣና ፎረም ከፊታችን ጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)11ኛው የጣና ፎረም ከጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በባሕር ዳር እና አዲስ አበባ ከተሞች ይካሄዳል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በሰጡት መግለጫ ፥ ፎረሙ “አፍሪካ በተለዋዋጩ ሉላዊ ሥርዓት” በሚል መሪ ሃሳብ በሶስት መድረኮች ይካሄዳል ብለዋል።
የመጀመሪያው መድረክ በባሕር ዳር የሚካሄድ ሲሆን ÷ 2ኛው በአዲስ አባባ ዓደዋ ድል መታሰቢያ እንዲሁም 3ኛው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሳባ እንደሚከናወን ተናግረዋል።
በመድረኩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት፣ ዲፕሎማቶች፣ የባለብዙ ወገን ተቋማት እና ልዩ መልዕክተኞ ይሳተፋሉ።
በፎረሙ አፍሪካውያን በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ተወናይ እንዲሆኑ የሚያስችል ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version