አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያስገነባው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ ሬድዮ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርጌኖ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ሬዲዮ ጣቢያው ዩኒቨርሲቲው የሚሰራቸውን ሥራዎች እንዲሁም የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህልና እሴት ለሌሎች ለማስተዋወቅ ፋይዳ አለው።
ዩኒቨርሲቲው በምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም በመማር ማስተማር ዘርፉ እያከናወነ ያለውን ተግባር ጨምሮ አካባቢያዊና ዓለም አቀፍ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋልም ነው ያሉት።
የሬዲዮ ጣቢያ ስቱዲዮ ዘመኑን የሚመጥን የሚዲያ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ በሚዲያው እንዱስትሪ ያካበተውን አቅም የሚያሳይ እንደሆነና ተቋሙ በዘርፉ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይነት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዶኒያስ ወ/ዓረጋይ በበኩላቸው÷ የሬዲዮ ጣቢያው ፋና በሚዲያ እንዱስትሪ ያካበተውን ልምድ ወደ ማህበረሰብ የማውረድ ሥራን እየሰራ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝና በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች መሰል የማስፋፋት ስራዎችን እንደሚሰራ አመላክተዋል።
ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያለው የአብሮነት ስራ እንደሚቀጥል እና የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የሚረዱ ሥልጠናዎችም እንደሚሰጡ አቶ አዶኒያስ ተናግረዋል።
በፍሬው አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!