Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጀመሪያ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል አቤል ያለው በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ዳንላንድ ኢብራሂም የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጫዋች አቤል ያለው ላይ በሰራው ጥፋት 53ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

የፋሲል ከነማን ጎል በረከት ግዛው ሲያቆጥር ዘላለም አበበ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

Exit mobile version