Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

47 ኪሎ ግራም አደንዛዠ እፅ ወደ አዲስ አበባ ይዘው የገቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 47 ኪሎ ግራም አደንዛዠ እፅ ወደ አዲስ አበባ ይዘው የገቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አሮጌው ኬላ አካባቢ ሁለት ተጠርጣሪዎች 47 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፁን ይዘው ሲንቀሳቁ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
 
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን ደረጀ ቱሉ ተጠርጣሪዎቹ ተከሳሾቹ የኬላ መንገዱን አሳብረው መንገድ በመቀየር በባጃጅ ጭነው ሲንቀሳቀሱ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አብራርተዋል፡፡
 
ኮሚሽኑ አደንዛዥና ሱስ አስያዥ ዕፆች በሰው ልጆች ላይ ከሚያሳድሩት የጤና መታወክ ባሻገር ለወንጀል መከሰት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን ገልጿል።
Exit mobile version