አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሌ ዞን መልከዓ ምድር ከቱሪዝም መስህብነት ባለፈ እምቅ የማዕድን ሃብት ያለበት ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ጁነዲን ሳዶ በወቅቱ እንዳነሱት፤ የሶፍ ዑመር ዋሻ እና የባሌ ተራሮችን ብሔራዊ ፓርክ የመሳሰሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን የያዘው የባሌ ዞን እምቅ የማዕድን ሃብት አለው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈጠሩት የልማት እንቅስቃሴ የአካባቢውን እምቅ አቅም የገለጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአካባቢው የማዕድን ሀብት ጥናት በስፋት መካሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በአካባቢው ያለው እምቅ የማዕድን ሃብት በጥናት ተደግፎ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለሀገሪቱ ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።
የቀድሞ አመራር ኩማ ደመቅሳ በበኩላቸው፤ በባሌ ዞን የተመለከቱት የተፈጥሮ ሃብት ከገመቱትም በላይ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን ሀብት ይዞ ደሃ መሆን የሳፍራል ብለዋል።
እነዚህን ተደብቀው የነበሩ ሃብቶች መንግስት በፍጥነት እና በጥራት ያለማበት መንገድ አስገራሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የተጀመሩት ስራዎች የተከበረችና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት እንደሚቻል ያሳዩ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ናቸው ብለዋል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!