Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሦስተኛ ዙር መርሐ ግብር ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ፈርሚን ሎፔዝ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራ ሲሆን፥ ማርከስ ራሽፎርድ (2) እንዲሁም ላሚን ያማል ቀሪዎቹን የባርሴሎና ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

በጨዋታው ኤል ካሀቢ ለኦሎምፒያኮስ ያስቆጠራት ግብ የግሪኩ ክለብ በዚህ የውድድር ዓመት በሻምፒየንስ ሊጉ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች የተገኘች ብቸኛ ግብ ሆናለች፡፡

በሌላ ጨዋታ ካይራት አልማቲ ከፓፎስ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቅቋል፡፡

አርሰናል ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ባየር ሊቨርኩሰን ከፒኤስጂ፣ ቪያሪያል ከማንቼስተር ሲቲ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version