አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከጁቬንቱስ እንዲሁም የጀርመኑ አይንትራክት ፍራንክፈርት ከእንግሊዙ ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ተጠባቂው የሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስ ጨዋታ በሳንቲያጎ ቤርናብዩ ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ሪያል ማድሪድ ባለፉት ሁለት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ድል የቀናው ሲሆን÷ ጁቬንቱስ በአንጻሩ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቅቋል።
የጣልያኑ ጁቬንቱስ ምንም እንኳን የታላቅ ታሪክ ባለቤት ቢሆንም ክለቡ አሁን ላይ እያሳየ ያለው ደካማ ብቃት ግን ለሪያል ማድሪድ ቀላል ተጋጣሚ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ወደ ጀርመን ተጉዞ ከአይንትራክት ፍራንክፈርት ጋር የሚጫወተው ሊቨርፑል ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው ተመላክቷል፡፡
በሁሉም ውድድሮች በተከታታይ 4 ጨዋታዎችን የተሸነፈው የአንፊልዱ ክለብ የዛሬውን ጨዋታ የሚሸነፍ ከሆነ በተከታታይ 5 ጊዜ በመሸነፍ ከፈረንጆቹ 1953 ወዲህ አስከፊ ውጤት በማስመዝገብ የራሱን ታሪክ ያሻሽላል፡፡
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በፕሪሚየር ሊጉ ብሎም በሻምፒየንስ ሊጉ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ የማይገኘው ሊቨርፑል የዛሬውን ግጥሚያ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ የጣልያኑ አታላንታ ከስላቪያ ፕራግ፣ ባየር ሙኒክ ከቤልጂዬሙ ክለብ ብሩገ፣ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከአያክስ አምስተርዳም፣ ሞናኮ ከቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም ስፖርቲንግ ሊዝበን ከማርሴይ ይጫወታሉ፡፡
ቀደም ብሎ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ደግሞ የስፔኑ አትሌቲክ ክለብ ከአዘርባጃኑ ካራባግ እንዲሁም የቱርኩ ጋላታሳራይ ከኖርዌዩ ቦዶ ግሊምት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!