አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሰላምን የማፅናት ተግባርን አጠናክሮ ቀጥሏል አሉ ሜጀር ጄኔራል አድማሱ አለሙ።
“ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በወልዲያ ከተማ ተካሂዷል።
የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ሜጀር ጄኔራል አድማሱ አለሙ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጽንፈኛውን ቡድን ከአካባቢው የማፅዳት ተግባር በውጤታማነት ቀጥሏል።
ሠራዊቱ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሰላምን የማፅናት ሥራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ ለዚህ ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አመልክተዋል።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው በበኩላቸው÷ ባዕዳን በራሳችን ወገኖች አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚያደርጉት ሙከራ እንደማይሳካ ተናግረዋል።
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብሬ÷ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና ተላላኪ ባንዳዎች በመቀናጀት የአካባቢውን ሠላም ለማደፍረስ እያደረጉት ያለውን ጥረት በጀግናው መከላከያና በሕብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ እየመከነ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰላምን አጽንቶ በማስቀጠል እድገትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ምሁራንና ሌላውም የሕብረተሰብ ክፍል ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመልክተዋል።
የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አበበ ግርማ (ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው መምህራን የአካባቢያውን ችግር ለመፍታት በእውቀትና በምርምር የታገዘ የመፍትሄ ሀሳብ ማፍለቅ ይጠበቅብናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!