Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር አዳሙ እና በፍቃዱ አለማየሁ አስቆጥረዋል፡፡

ነገሌ አርሲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ገ/መስቀል ዱባለ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከፋሲል ከነማ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ሲሆን÷ ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ  ከተማ  ደግሞ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

Exit mobile version