Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጣሊያን ለቱኒዚያ በህገ- ወጥ መንገድ የሚገቡ ስደተኞችን ለመከላከል 13 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጣሊያን ለቱኒዚያ በህገ-ወጥ መንገድ ባህር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞችን ለመከላከል የሚውል የ13 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች።
 
ድጋፉ ቱኒዚያ የባህር ድንበሯን ለማጠናከር እንዲረዳትና በትናንሽ ጀልባዎች ሜዴትራኒያን ባህርን አቋርጠው የሚመጡ ስደተኞችን ለማስቆም ያለመ ነው ተብሏል።
 
የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉኢጂ ዲ ማዮ ቱኒስን በጎበኙበት ወቅት ÷በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጣሊያን ለሚገቡ ሰዎች ሀገራቸው ቦታ እንደሌላት ገልጸዋል።
 
አያይዘውም ችግሩን ለመቅረፍ ሀገራቸው የቱኒዝያን የየብስ እና የባህር ሀይሎችን ለማሰልጠን መዘጋጀቷን ተናግረዋል ።
 
ጣሊያን በደቡባዊ ዳርቻዎች በየቀኑ የሚመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ጫና ለመቋቋም እየሰራች ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ምክንያት ሥራው እየተወሳሰበ መምጣቱ ተነግሯል።
 
ምንጭ፡- ቢቢሲ
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version