Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ጌታቸው ረዳ የስምረት ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ አቶ ጌታቸው ረዳን ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

ፓርቲው መስራች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያካሂድ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ሰባት  ጉዳይ ፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም 31 የምክር ቤት አባላትን መርጧል፡፡

በዚህም መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ፣ ነጋ አሰፋ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ሃፍቱ ኪሮስ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሰብለ አሰፋ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።

በተመሳሳይ የቁጥጥር ኮሚሽን እና ኢንስፔክሽን ሊቀመንበር አቶ ገብረሕይወት ገብረስላሴ እንዲሁም አብረሃለይ አበራ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

በነፃነት ፀጋይ

Exit mobile version