Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለሀገር ለሚያስፈልግ ነገር ሁሉ መትጋትና መከታተል ያስፈልጋል – ዶ/ር መቅደስ ዳባ 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሀገር ስኬት ለሚያስፈልግ ነገር ሁሉ መትጋትና መከታተል ያስፈልጋል አሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ።

የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንደ ሀገር የተሻለ ስራ መሰራቱን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፤ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የፕሮጀክት ቅልጥፍና ውጤታማነት የታየበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ለግድቡ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በራስ አቅም ማምረት በመቻሉ ወጪና ድካምን መቀነስ ማስቻሉን መመልከታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሀገራቸውን የሚወዱ ሰራተኞችን መመልከታቸውን በማውሳት ይህም ከስራ ዕድል ፈጠራ ባሻገር ለስልጠና አቅም መሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

የቆመን ፕሮጀክት ነፍስ መዝራት መቻል ትልቅ የአመራር ክህሎትና ጥበብ የሚጠይቅና ይህም የታየበት ነው ብለዋል፡፡

Exit mobile version