Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስቴሩ በሐረር ከተማ በ20 ሚሊየን ብር ወጪ ለአቅመ ደካሞች ያስገነባቸውን ቤቶች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሐረር ከተማ በ20 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባቸውን ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ሙክታር ሳሊህ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መርሐ ግብሩ ስምንት አቅመ ደካማ አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው።

የክልሉ መንግሥትም መሰል ተግባራት በተለያዩ ዘርፎች እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሚኒስቴሩ ጥራትና ፍጥነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ላከናወነው መልካም ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የከተማና መረሰተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ በበኩላቸው÷ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖችን ህይወት እንዲሻሻል እያደረገ ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩም በሀረር ከተማ በ20 ሚሊየን ብር ወጪ ደረጃውን የጠበቀና የዜጎችን ክብር በሚመጥን ደረጃ የመኖሪያ ቤት ከመገንባት ባለፈ አስፈላጊ የቤት ቁሳቁስ ማሟላቱን አንስተዋል።

በቀጣይም ሚኒስቴሩ ከመደበኛ ስራው ባሻገር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version