👉 በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር በሚፈጽሙ ኃይሎች ላይ የመንግሥትን ኃይል በብቸኝነት የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፣
👉 የሕወሃት ቡድን የፕሪቶሪያዊያውን ስምምነት ወደ ጎን በመተው ከጦርነቱ አዙሪት ላለመውጣት ባላቸው ፍላጎት በሌሎች ክልሎችም ያሉ ጽንፈኛ ቡድኖች እና ከኢትዮጵያ ቋሚ ጠላቶች ጋር በማበር ሕዝብን ወደ ስቃይ ለማስገባት በየቀኑ የጦርነት ድግስ ሲያወጁ ይስተዋላል፤ ይህንን ጦር ሰባቂ ቡድን አደብ ለማስገዛትና ጊዜያዊ አስተዳደሩን በማገዝ ክልሉ ሰላማዊ እንዲሆን ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 ሉዓላዊነትን ለመዳፈር የሚደረገውን የሻዕቢያ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተሰራ ያሉ ስራዎችና አሁናዊ የትግራይ ክልል የሰላም፣ ጸጥታና ፖለቲካ ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራሪያ ቢሰጥ፣
👉 አካታች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ከማን ምን ይጠበቃል እንዲሁም በምክክር ሂደቱ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ ጥቂት የፖለቲካ ኃይሎችን በተመለከተ የመንግሠት አቋም ቢብራራ፣
👉 የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደቱና የመጪው ጊዜ ተስፋ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፤
👉ሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቷን በአግባቡ ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ የጋዝ ምርትና ሎሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን መጀመሯ ትልቅ ብስራት እንደመሆኑ መጠን የውጭ ምንዛሪን ከማዳን ረገድ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራና ሀገሪቱን ከተረጂነት በማላቀቅ ነጋችንን ከመበየንና አጠቃላይ ኢኮኖሚያችንን ከማነቃቃት አኳያ ያላቸው ፋይዳ በዝርዝር ቢገለጽ፤
👉ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተው ለዜጎች እንደሚተላለፉ ተገልጿል፤ ዕቅዱ እንዲሳካ በመንግሥት በኩል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፤
👉የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነት ችግር በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የሚታዩ ሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ቀጣይ ሊሰሩ የታሰቡ ሥራዎች ዙሪያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፤
👉የመንግሥት ሰራተኞችን ደመወዝ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በመሰረታዊ ሸቀጦችና በቤት ኪራይ ላይ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት በመኖራቸው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች በኑሮ ውድነት እየተጎዱ ናቸው፤ የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት ለመፍታትና ሕገወጦችን በመቆጣጠር ርምጃ ከመውሰድ አንፃር እየተሰሩ ባሉ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

