አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር በነገው ዕለት ይጀመራል።
በ19 የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄደው 2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በወጣቶች ኦሊምፒኩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ነገ የሚጀምሩ ሲሆን፥ 187 ወንዶች እና 185 ሴቶች በድምሩ 372 አትሌቶች ይሳተፋሉ።
በነገው ዕለት የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድርን ጨምሮ ሌሎች የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይካሄዳሉ።
በውድድሩ ላይ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን፥ እስከ ጥቅምት 23/2018 የሚቀጥል ይሆናል፡፡

