Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ውክልና በሌለው አካል ያጣችውን የባሕር በር የመጠየቅ መብት አላት – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በተንኮል እና ውክልና በሌለው አካል ያጣችውን የባህር በር የመጠየቅ ህጋዊም ሆነ ታሪካዊ መብት አላት አሉ የሕግ ምሁራን።

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራኑ፤ ወሰኗ ባሕር የነበረችው ኢትዮጵያ የግዙፍ ባሕር ኃይል ባለቤት ነበረች ብለዋል።

የሕግ ባለሙያው አበረ አዳሙ እንደተናገሩት፤ ከ30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ ሕጋዊ መሰረት የለውም።

እንደ ሀገር ህዝብ ሳይወከል እና ሳያውቅ የተላለፈው ውሳኔ የሀገር ክህደት እንደሆነ አስረድተዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በሴራ እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ያጣችውን የባሕር በር መልሳ እድታገኝ ታሪክ እና ህግ ይደግፋታል ነው ያሉት።

የዓለም አቀፍ የውሃ ህግ ባለሙያ ከበደ ገርባ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዓለም አቀፉ ህግ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘርፈብዙ ጥቅሞች ያሉትን የባሕር በር ለማግኘት ኢትዮጵያ ያነሳችው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ገልጸው፤ ጥያቄው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ይሁንታ እያገኘ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ሕጋዊ መሠረት፣ ታሪካዊ እና የሰነድ ማስረጃዎችን በተገቢው በመሰነድ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጥያቄዋ እንዲመለስ ጥረቷን አጠናክራ መቀጠል እንደሚጠበቅባት ምሁራኑ አስገንዝበዋል።

በታሪኩ ለገሰ

Exit mobile version