አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 21ኛውን ኤርባስ ኤ350-900 አዉሮፕላን (ET-BCE) በዛሬው ዕለት ተረክቧል።
አየር መንገዱ ኤርባስ ኤ350-900 አውሮፕላን መረከቡ ለመንገዶኞቹ የሚሰጠውን ዘመናዊና ምቹ አገልግሎት በተሻለ መንገድ የሚያጠናክር እንደሆነ ገልጿል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ያለውን የመሪነት ሚና የሚያስቀጥል እንደሆነ አስታውቋል።
የአየር መንገዱ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።

