Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢንዱስትሪ ምርቶችን ተወዳዳሪነት የሚያሳድገው የኢትዮጵያ ታዳሸ ኃይል ልማት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የጀርመን ተጠባባቂ አምባሳደር ፈርዲናንድ ቮን ዌይ የኢትዮጵያ የታዳሸ ኃይል ልማት የኢንዱስትሪ ምርቶቿን ደረጃ በማሳደግ በአውሮፓ ገበያ ያላትን ተወዳዳሪነት ይጨምራል አሉ።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፍ ማሻሻያዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸው፤ ማሻሻያዎቹ ከዲጂታላይዜሽን እና ፈጠራ ጋር ተያይዘው ይሄዳሉ ብለዋል።
በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የኢኮኖሚ ለውጦች ለወጣቶች፣ ለፈጠራ ባለሙያዎች ሃሳባቸውን በትክክል ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስችሉ መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል የሰጠችውን ትኩረት አድንቀው፤ የውሃ፣ የንፋስ፣ የጂኦተርማል እና የፀሐይ ኃይል አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በታዳሸ ኃይል የምታከናውናቸው ተግባራት የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ምርቶችን ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተናግረዋል።
ከእነዚህ የኃይል ምንጮች የሚወጡ ምርቶች በአውሮፓ ገበያ ተወዳዳሪነታቸው ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እና ጀርመን በርካታ ዓመታት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አመልክተው፤ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት በበርካታ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚሰሩ በመካከላቸው ትልቅ ትብብር እና መተማመን እንዳላቸው ገልጸዋል።
የግብርና እና የገጠር ልማት ስራዎች ለዚህ የትብብሩ ማሳያ መሆኑን በአብነት አንስተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version