አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና በቤጂንግ እና ሆንዙ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሆንዙ የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ በ2:24:29 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች።
በወንዶች አትሌት ጫሉ ደሶ በ2:11:15 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል።
በተመሳሳይ በቤጂንግ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2:08:10 በመግባት ሲያሸንፍ÷ አትሌት ደሳለኝ ግርማ ሁለተኛ ወጥቷል።
በሴቶች አትሌት አንቻሉ ደሴ በ2:26:06 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ÷ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ቁፍቱ ጣሂር ሦስተኛ ወጥታለች።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

