Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመኸር ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በ2017/18 የመኸር ወቅት ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራ ተጀምሯል አለ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በመኸር ወቅት 763 ሺህ 424 ሄክታር መሬት በዓመታዊ ሰብሎች ተሸፍኗል።

አሁን ላይ የምርት አሰባሰብ ስራ መጀመሩን ገልጸው÷ እስካሁን በዓመታዊ፣ አዝርዕትና ሆርቲካልቸር ሰብሎች 23 ሺህ 312 ሄክታር መሬት ላይ የተዘራው ምርት መሰብሰቡን ጠቁመዋል።

በዚህም እስካሁን ከተሰበሰበው 19 ሺህ 161 ሄክታር መሬት ላይ 1 ሚሊየን 148 ሺህ 533 ኩንታል ምርት መገኘቱን አንስተዋል።

በምርት ዘመኑ ከዓመታዊ ሰብሎች ከ36 ሚሊየን 640 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱንም አመላክተዋል።

በተጨማሪም ከፍራፍሬ ሰብሎች እስካሁን በተሰራው ስራ 344 ሺህ 750 ኩንታል እና ከእንሰት ሰብል እስካሁን 375 ሺህ ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸው÷ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በምርት አሰባሰብ ወቅት ብክነት እንዳይኖር በባለሙያዎች የክትትል እና ድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version