አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአራተኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዳማ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የአዳማ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቢኒያም አይተን በመጀመሪያው አጋማሽ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
በዚህም አዳማ ከተማ ከተከታታይ የአቻ ውጤት በኋላ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል ማሳካት ችሏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲም በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ሲሞን ፒተር እና ድልአዲስ ገብሬ (በራስ ላይ) ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይገናኛሉ፡፡

