Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሕይወት መሃመድ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ም/ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሕይወት መሐመድ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

‎የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

በዚህ ወቅትም ጉባዔው የኢትዮጽያ ባሕል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሕይወት መሐመድን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በሙሉ ድምፅ መርጧል።
‌‎
የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን የአባልነት ጥያቄን በይፋ ተቀባይነት ያገኘችው ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያውን የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

በዝምባብዌ ሐረሪ ‎ለ2 ቀናት የተካሄደው ጉባዔው አፍሪካን በባሕላዊ ስፖርቶች ለማስተሳሰርና አንድነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተመራጯ ሕይወት መሐመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version