Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተጠባቂው የማንቼስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ፍልሚያ…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ተጠባቂው የማንቼስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ፍልሚያ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ይደረጋል፡፡

በሳምንቱ አጋማሽ በሻምፒየንስ ሊግ ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት የቻሉት ሁለቱ ቡድኖች ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ በምሽቱ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በእርስ ባደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሊቨርፑል ሁለቱን በማሸነፍ የበላይነት አለው፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በአንዱ ጨዋታ ድል ሲቀናው በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡

የምሽቱ ጨዋታ ለአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው 1000ኛ ጨዋታቸው ሲሆን፥ በዚህም 1ሺህ እና ከዚያ በላይ ጨዋታዎችን ከመሩ አሰልጣኞች ተርታ ስማቸውን ያሰፍራሉ፡፡

በሌሎች የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ከኒውካስል፣ አስቶን ቪላ ከቦርንማውዝ፣ ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ 11 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ቶተንሃም ከማንቼስር ዩናይትድ እንዲሁም ሰንደርላንድ ከአርሰናል በተመሳሳይ 2 ለ 2 አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ ቼልሲ ወልቭስን 3 ለ 0፣ ኤቨርተን ፉልሃምን 2 ለ 0 ፣ ዌስትሃም በርንሌይን 3 ለ 2 አሸንፈዋል፡፡

Exit mobile version