አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማሌዢያ እና ታይላንድ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ የጠፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በአንድ ትልቅ ጀልባ መነሻቸውን ከማይናማር ቡቲዳንግ ከተማ ያደረጉ 300 ያህል ሰዎች ወደ ድንበር ሲደርሱ ወደሌሎች ሦስት መለስተኛ ጀልባዎች እንዲሄዱ መደረጉን የማሌዢያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ከእነዚህ ሦስት ጀልባዎች መካከል በአንደኛው ላይ ባጋጠመው የመስጠም አደጋ እስካሁን 10 ሰዎችን በህይወት ማግኘት የተቻለ ሲሆን፥ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፡፡
አደጋው ከሦስት ቀናት በፊት የደረሰ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ሁለት ጀልባዎች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅና የጠፉ ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

