አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራትን በተሻለ ፍጥነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ይሰራል አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ባለፉት 10 ቀናት የተከናወኑ ተግባራትን በገመገሙበት ወቅት÷ በተቋማትና ወረዳዎች የተሻለ አፈጻጸም ቢኖርም አዝጋሚ ሥራዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ውስንነቶችን በማስተካከል እንዲሁም ሥራዎችን በጥራትና ፍጥነት በማከናወን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።
በዚህ መሰረትም የኑሮ ውድነት፣ ሌብነት፣ መንደርተኝነት እና ጠባቂነትን ለመቀነስ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ ነው ያሉት አቶ ኦርዲን።
በተጨማሪም ተረጂነት፣ የማይታረስ መሬት፣ ተፈናቃይ፣ ኮንትሮባንድ እና ሽፍታን ለማስቀረት በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡
በገጠር ወረዳዎች የኮሪደር ልማት፣ የምርት ማከማቻ፣ የቱሪስት መዳረሻ፣ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት፣ አግሮ ፕሮሰሲንግና የሽያጭ ማዕከላት ግንባታ እንደሚከናውን ጠቁመዋል፡፡
ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም እርሻ፣ በበጋ እርሻ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኢንዱስትሪና ማዕድን ዘርፍ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ተቋማት ነጻና ገለልተኛ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የተጀመረው ሥራ እንደሚጠናከርም አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

