አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት በላይ ካሳ (ፕ/ር)፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው ።
ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል።
በመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተመላክቷል።
በሐይማኖት ወንድራድ

