አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን በእጅጉ የሚቀርፍ 232 ነጥብ 84 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የነባር ኤሌክትሪክ መስመሮች የመልሶ ግንባታና የአዲስ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራ ተጠናቅቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ሪጅን ኦፕሬሽን ኮኦርዲኔሽን ጽ/ቤት በሩብ ዓመቱ ከተከናወነው የኤሌክትሪክ መስመር መልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ስራ 105 ነጥብ 38 ኪሎ ሜትር የነባር ኤሌክትሪክ መስመር የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ እንደሚገኝበት ተመላክቷል።
127 ነጥብ 46 ኪሎ ሜትር ደግሞ የአዲስ መስመር ማስፋፊያ መሆኑን የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች የ130 ትራንስፎርመሮችን አቅም በማሻሻልና 210 አዳዲስ ትራንስፎርመሮችን በመትከል ለከተማው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖርና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
ለኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ 3 ሺህ ግኝቶች ላይ የቅድመ ጥገና ሥራ ለመስራት ታቅዶ በ2 ሺህ 914 ግኝቶች ላይ የማስተካከል ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ካሉት 36 መጋቢ የምድር ስር ተቀባሪ መስመሮች መካከል 24 የምርመራ ስራ ተሰርቶላቸው ጥገናቸው ተጠናቅቋል ብለዋል፡፡
ቀሪዎቹ 12 መጋቢ መስመሮች በሁለተኛው ሩብ ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።
ከትራንስፎርመሮች ምርመራ ጋር በተያዘዘ የሩብ ዓመቱ መባቻ ድረስ 13 ሺህ 205 ትራንስፎርመሮችን ለመመርመር ታቅዶ 12 ሺህ 702ቱ ላይ ምርመራ ተደርጎ የጥገና ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ሪጅን ማስተባበሪያ 31 የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያዎችን ተጠቅሞ በተለያዩ የታሪፍ መደብ ለሚገኙ ከ1 ሚሊየን 55 ሺህ በላይ ደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተጠቅሷል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

