Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱሪስት ፍሰትን የሚጨምረው የመዳረሻዎች ልማት …

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት የቱሪስት ፍሰትን ለመጨመር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ።

የቢሮው ምክትልና የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ለማ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በክልሉ ትላልቅ የቱሪስት መዳረሻዎች በመልማታቸው ዘርፉ እየተነቃቃ ይገኛል።

በክልሉ በርካታ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን አንስተው÷ የማልማት፣ የማስተዋወቅና አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን የማሟላት ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸው÷ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ከ500 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን መጎብኘታቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም ከ338 ሚሊየን 800 ሺህ ብር በላይ ቀጥተኛ ያልሆነና 373 ሺህ 297 ብር ከጥበቃ ቦታዎች በደረሰኝ ገቢ መሰብሰቡን ጠቁመዋል።

በዘርፉ ባለፉት ሦስት ወራት ለ1 ሺህ 493 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯልም ነው ያሉት።

ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ፣ ኦሲቃ ፍል ውሃ፣ የሱሪ ማህበረሰብ ቱሪዝም እንዲሁም በክልሉ የተከበሩ የተለያዩ ክብረ በዓላት ለቱሪዝም ፍሰት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደነበራቸው አመላክተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version