አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈጽሟል።
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) አስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ከተካሄደ በኋላ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የላጲሶ (ፕ/ር) ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል።
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምና ሲከታተሉ ቆይተው ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡
ላጲሶ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተው አልፈዋል።

