አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የከተማዋ ነዋሪ የሆነችው ተማሪ ሊዛ ደሳለኝ ላይ የግድያ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል አለ።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ እንዳስታወሱት፤ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ተማሪ ሊዛ ደሳለኝ ተገድላ ተገኝታለች።
የተፈጸመውን የወንጀል ድርጊት ተከትሎ የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተደራጅቶ ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል ነው ያሉት።
በዚህም ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በግድያ ወንጀሉ የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።
በመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ተሾመ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ተጠርጣሪው ሞባይል ስልክ ለመቀማት በሚል የፈፀመው ድርጊት መሆኑን በመግለጽ የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል ብለዋል።
ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ በመቀጠል ቀሪ የምርመራ ስራዎችን እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።
በስንታየሁ አራጌ

