Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሪደር ልማቱ ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአካባቢው ውጤት የሆኑ ወጪ ቆጣቢ የመንገድ ዳር መብራቶችን ለኮሪደር ልማት ሥራው በግብዓትነት በመጠቀም ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

በክልሉ በላቀ ቁጭትና ቁርጠኝነት እየተሰራ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ግለቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ሐረር ዜጎች እንደልብ የሚንቀሳቀሱባት ከተማ እንድትሆን የመብራት ገጠማና ጥገና ሥራ እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የእረፍት ቀናትን ጨምሮ ቀንና ማታ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የዛሬ ትጋት ሁነኛ ማሳያ መሆናቸውንም አቶ ኦርዲን አመልክተዋል፡፡

Exit mobile version