Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንገድ ደህንነትን በማረጋገጥ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ ነው አሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፡፡

የአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቀን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ እየደረሰ ያለው የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ በመሆኑ ኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ርምጃዎችን እየወሰደች ነው።

ለአብነትም በተለያዩ ከተሞች እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የመንገድ ደህንነት እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህም እየተገነቡ ያሉ የእግረኞች፣ የብስክሌት እንዲሁም የተሽከርካሪ ምቹ መንገዶች የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደሚረዱ አመልክተዋል፡፡

የመንገድ ደህንነትን የሚያስጠብቁ የህግ ማዕቀፎች መውጣታቸውን አስታውሰው፤ ለትራፊክ አደጋ መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ መተቦጌ በበኩላቸው በአፍሪካ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ የጀመረችው የሚበረታታ ጥረት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በአፍሪካ የመንገድ ደህንነትንና ዘላቂ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ የሚከሰተውን ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመንገድ ደህንነት ቀን የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች እንደሚታወሱ በመጠቆም በ2030 በአህጉሪቱ በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን ሞት በ50 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ 2012 ባሳለፈው ውሳኔ ቀኑ በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን እለቱ ከዓለም የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች መታሰቢያ ቀን ጋር እንዲተሳሰር ተደርጓል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version