አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ንጋቱ ገ/ስላሴ (በራሱ ላይ) በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 12 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሠንጠረዡ 2ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡
የባለፈው የውድድር ዓመት የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በበኩሉ በ5 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

