Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች ብዛት ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ዓቀፉ ኢንተርፕርነርሽፕ ኔትወርክ በየጊዜው በሚያወጣው የኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች ብዛት ኢትዮጵያ ቀዳሚ ሆናለች።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽንና አጋርነት ዳይሬክተር እመቤት ተጫኔ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ የዓለም ዓቀፉ ኢንተርፕርነርሺፕ ኔትወርክ የሀገራትን የኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች እየመዘገበ በየጊዜው ደረጃ ያወጣል።

ተቋሙ ባለፈው ዓመት ባዘጋጀው የዓለም ኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት ኢትዮጵያ በኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች ከአፍሪካ 2ኛ ከዓለም ደግሞ 8ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋን አስታውሰዋል።

ዘንድሮ ‘በጋራ እንገንባ’ በሚል መሪ ሀሳብ ለ12ኛ ጊዜ በሚከበረው የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት ኢትዮጵያ የተሻለ ደረጃ ትይዛለች ተብሎ እንደሚገመት ገልጸው፤ ሳምንቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ በዛሬው ዕለት በኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች ከዓለም ቀዳሚ ደረጃ ልትይዝ መቻሏን ተናግረዋል።

ይህ ውጤት ሊመጣ የቻለው የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመቀናጀት በሰራው ስራ መሆኑን አመልክተዋል።

በኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንቱ ስልጠና፣ ጉባኤ፣ የልምድ ልውውጥ፣ የገበያ ትስስርና የፖሊሲ ውይይት የመሳሰሉ ሁነቶች እንደሚከናወኑ ገልጸው፤ የዓለም ዓቀፉ ኢንተርፕርነርሺፕ ኔትወርክ ኢትዮጵያ 4 ሺህ 375 ሁነቶችን በማዘጋጀት በዛሬው ዕለት በቀዳሚነት እንዳሰፈራት ጠቁመዋል።

ከኢትዮጵያ በመቀጠል ብራዚል እና ዮርዳኖስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ መያዛቸውን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ደረጃዋን አስጠብቃ እንድትቀጥል ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም በኢንተርፕርነርሺፕ ሁነቶች በቀዳሚነት መመረጧ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እና ከተለያዩ ሀገራት ኢንተርፕርነሮች ጋር ትስስር ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version