Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አገልግሎቱ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች 33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ባለፉት አራት ወራት ከተለያዩ የገቢ አማራጮች 33 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) ÷ ገቢው ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም በዕቅድ ለመሰብሰብ ከተያዘው 33 ነጥብ 72 ቢሊየን ብር አንፃር 97 ከመቶ አፈፃፀም እንዳለው ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

ከኢነርጂ ሽያጭ ብቻ 22 ነጥብ 21 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቁመው÷ ከዕቅዱ አንፃር 99 ከመቶ መፈጸሙን አመልክተዋል፡፡

ባለፉት አራት ወራት 153 ሺህ 973 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል።

የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማጠናከር እየተደረገ ባለው ጥረት በጥቅምት ወር በዲጂታል ክፍያ አማራጮች ክፍያ የፈፀሙት ደንበኞች ቁጥር 95 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version