አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሥራ ጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሕብረተሰቡ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎቶችን በቀላሉ በአንድ ቦታ እንዲያገኝ ያስችላል፡፡

