ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ በሚገኙ ባለድርሻ አካላት መካከል ለተፈጠሩ አለመግባባቶች በመነጋገር መፍትሔ እንዲመጣ የሚያደርግ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ነው፡፡
ሂደቱ ተከናውኖ አመርቂ ውጤት ባስመዘገበባቸው ሀገራት ባለድርሻ አካላት በሀገራዊ ምክክር የጋራ አቅጣጫን በማበጀት አንኳር በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ሀገራዊ መግባባትን ፈጥረዋል፡፡
ታዲያ በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ውስጥ በተወካዮቻችንን አማካኝነት ስንሳተፍ የጋራ መንገዶችን (Common Ground) መስርተን ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የትኞቹ ተግባራት ከተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ይጠበቃሉ?
1. የጋራ እሴቶችን መፈለግ
በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ ዜጎች አንድ የሚያደርጓቸው እሴቶቻቸው ላይ ማተኮራቸው በሂደቱ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያደርጉትን ጉዞ ፍሬያማ ያደርገዋል፡፡
የሰው ልጆች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስፈልጋቸውን ክብር፣ ፍትሕ እና እንዱ ለሌላው መኖር ለሀገር አንድነት አስፈላጊ መሆናቸውን በመረዳት፤ እነዚህንም እንደመርህ መከተል የጋራ አቅጣጫን ለመተለም በእጅጉ ያግዛል፡፡
2. ከተለያዩ አቋሞች ጀርባ ያሉ ፍላጎቶችን መረዳት
የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ወደ ምክክር መድረኮች ሲመጡ የተለያዩ አቋሞችን ሊያንፀባርቁ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ጥቂት የማይባሉ ባለድርሻ አካላት በእጅጉ የሚራራቅ አቋም መያዛቸው መግባባት ላይ ለመድረስ የሚደረገውን መንገድ ረዥም ያደርጉታል፡፡
ሆኖም ግን አፅዕኖት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ እነዚህ አቋሞች መነሻቸው ያልተመለሱ እና ቁርሾን የፈጠሩ የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች መሆናቸው ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ማድረግ አንዳችን የሌላችንን ሕመሞች እና ፍላጎቶችን በመረዳት የጋራ አቅጣጫን ለመተለም በእጅጉ ይረዳል፡፡
3. ለትንንሽ ስኬቶች ዕውቅና መስጠት
የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ረጅም እና የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚፈልጉ ከመሆናቸው አንፃር እጅግ በርካታ ጉዳዮች በሂደቱ ተነስተው ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡
ሆኖም ግን ሂደቱ የሚፈጥራቸውን ትንንሽ ስኬቶች አጉልቶ በማየት እና ከተገኙ ስኬቶች በመነሳት ትልልቅ እና ውስብስብ ችግሮችን መፍታት ሂደቱን ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ ይህም የጋራ አቅጣጫ ለመተለም የሚደረገውን ጥረት ያጠናክረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

