Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለኢንተርፕርነርሽፕ ያላትን ምቹ ሁኔታ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ከሕዳር 8 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን መርሐ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል፡፡

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ዓለም አቀፍ እንግዶች እና የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል።

ሙፈሪሃት ካሚል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መርሐ ግብሩ የእስካሁን ሥራዎቻችንን የምናይበትና በቀጣይ በተሻለ አቋም ለመዘጋጀት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟን ከፍ አድርገው ያስጠሩ ሥራ ፈጣሪዎች ያሉባት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሯ÷ የሃሳብ ብዝሃነት ያለባት ሀገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለፈጠራ ምቹ እንደሆነች አውስተዋል፡፡

ለፈጠራ ምሕዳር ተግዳሮት የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ባለፉት ዓመታት በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ኢንተርፕርነሮች ለችግሮቻችን አዳዲስ መፍትሔዎችን የሚያፈልቁ ፈር ቀዳጅ እና ባለራዕዮች ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኢንተርፕርነርሽፕ ሁነቶችን በማዘጋጀት ብራዚልን በመቅደም ከዓለም አንደኛ መሆኗን አመልክተዋል፡፡

ኢንተርፕርነሮች ሀገር ሰሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው÷ በዘንድሮው 12ኛው የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት ስልጠናዎች፣ የፈጠራ ሃሳብ ውድድሮችና ጥናቶች ይከናወናሉ ብለዋል።

በሶስና አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version