አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከበርካታ ዓመታት በኋላ የፖርቹጋል እና አሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ለሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓመታት በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት ጨዋታ እንደሚያደርግ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
ሮናልዶ በአሜሪካ ምድር ለመጨረሻ ጊዜ የተጫወተው በፈረንጆቹ 2014 ማንቼስተር ዩናይትድ ከሪያል ማድሪድ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በወቅቱ የማንቼስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድን የወዳጅነት ጨዋታ ከ109 ሺህ በላይ ተመልካቾች ስታዲየም በመገኘት ተመልክተዋል፡፡
አምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው በቅርቡ ከፒርስ ሞርጋን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በመገናኘት ስለ ሰላም መወያየት እንደሚፈልግ መናገሩ ይታወሳል፡፡
ሀገሩ ፖርቹጋል ወደ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ ከዚህ የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ ሮናልዶ ወደ አሜሪካ የሚያቀና ይሆናል፡፡
የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ውድድር አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጋራ እንደሚያዘጋጁት ይታወቃል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

