Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፎረሙ ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሠራራት መልካም አሻራ ጥሏል – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሠራራት መልካም አሻራ ጥሏል አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ።

አቶ አወል በ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ እንዳሉት ÷ 10ኛው የከተሞች ፎረም የመደመር እሳቤ በተግባር የታየበት ነው፡፡

የፎረሙ ታዳሚዎች በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ ስኬታማ ቆይታ ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡

ፎረሙ ከተሞች ልምዳቸውን የተካፈሉበት አንዱ ከሌላው ትምህርት የወሰደበት መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡

ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሠራራት መልካም አሻራ መጣሉን ገልጸው ÷ ፎረሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version