አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ኤጀንሲ (ዩኤን ውመን) ሴቶች በሰላም ግንባታ ሒደት ላይ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ በትብብር መስራት ይገባል አለ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ም/ቤት በፈረንጆቹ 2000 ላይ ያጸደቀው የሴቶች ሰላምና ደህንነት ስምምነት ውሳኔ 1325፤ 25ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡
ስምምነቱ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሴቶች በሁሉም የሰላም ግንባታ ሒደቶች ላይ ንቁና ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መሰረት መጣሉ ተመላክቷል።
መርሐ ግብሩን ዩኤን ውመን ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት እና የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡
በዩኤን ውመን የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ስካድራክ ዱሳቤ በወቅቱ እንዳሉት ፥ የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን የሴቶችን አቅም ይበልጥ ማጎልበት ይገባል፡፡
ሴቶች በሚስተዋሉ የተለያዩ ግጭቶች ወቅትም ሆነ ከግጭት በኋላ ጾታን መሰረት ላደረጉ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
መሰል ችግሮችም ከጦርነት በኋላ በሚደረጉ የሰላም ግንባታ ሒደቶች ላይ በንቃት እንዳይሳተፉ ተግዳሮት ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡
የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ ሴቶች በዘላቂ የሰላም ግንባታ ሒደቶች ላይ ትርጉም ያለው ውክልና እንዲኖራቸው በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም መንግሥታት ሴቶች በመሰል ሒደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ባለድርሻ አካላት ሴቶች የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡ የግንዛቤ ፈጠራና ሌሎች ሥራዎችን በቁርጠኝነት መከወን እንዳለባቸውአመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ዳይሬክተር ሳባ ገብረመድህን ÷ የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ተቋማቸው ለማሕበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን አቅም ለማጎልበት በርካታ ሥራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ሴቶችን በሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የሰላም ውይይትና ድርድር ሒደቶች ላይ በሚገባ ማሳተፍ ላይ ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

