Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ25ኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን በነገው ዕለት ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች እንደሚዘጉ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት፡-

👉 ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ)
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ

👉 ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ)
👉 ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት)

👉 ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ)
👉 ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ)

👉 ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)
👉 ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ)

👉 ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
👉 ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)

👉 ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ)
👉 ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ)

👉 ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ)
👉 ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ)

👉 ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት)
👉 ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ)

👉 ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
👉 ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)

👉 ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
👉 ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ)

👉 ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
👉 ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
👉 ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)

ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን÷ በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚችሉም ተመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version